About Us

Messenger Alemayehu Gashaw (Alex)

International Director Of ETM From Ethiopia

The Vision Of ETM

To proclaim the Gospel Our Lord Jesus to this end time generation and preparing the Bride of Christ

 

መግቢያ

ልጆች ሆይ የመጨረሻ ሰአት ነው 1ዩ2፡18, 2ጴጥ3፡8-15, 1ተሰ4፡13-18, 1ተሰ5፡1-9, 1ዩሐ2፡28-29

በአገራችን አሁን ብዙ ነፍስ ወደ ቤ/ክ እየጨመሩ እና ብዙ ቁጥር ያላቸው ቤ/ክ እየተተከሉ ቢሆንም  በተለያዩ ስም የሚጠሩ መንፈሳዊ አገልግሎት የሚሰጡ አገልግሎቶች እየተጨመሩ እንደሆነ በግልፅ ቢታይም ነገር ግን በአገራችን ካለው ነባራዊ ሁኔታ እና ከአገሪቱ ህዝብ ቁጥር አንፃር ሲታይ  ገና ብዙ መስራት  እንዳለበት እናያለን ቁጥራቸው የበዛ ነፍሳት ቢጨመሩም ወደ መንፈሳዊ አገልግሎት በመስጠት ቤ/ክ የሚደግፍ አገልግሎት ቢኖሩም ብዙ ቤ/ክ በተለያዩ በአገሪቱ ቦታዎች ቢከፈቱም  በተለየ የአገልግሎት ቢሮዎች የሚያገለግሉ አገልጋዮች በብዛት ቢነሱም ነገር ግን አሁን በአገራችን እየታየ  ያለው የሚሰማው በየቤ/ክ እየሆነ ያለው ነገር የቅዱሳን ህይወት  የአገልጋዮች ሕይወት ከቃሉ  ሚዛን ዕለት ከዕለት እየወረደ መሄድ ወደ ቤ/ክ የተጨመሩትንም ነፍሳት ከጥራት አንፃር ሲታይ ደቀመዝሙር ከማድገር አኳያ  ገና ምንም እንዳልተሰራ የአማኞች ሕይወት   እና አኗኗር   በግልፅ ያሳየናል ብዙ ቁጥር ካላቸው አማኞች ውስጥ የደቀመዛሙርትነት ህይወት ተላብሰው የሚመላለሱ በጣት የሚቆጥሩ አገልጋዮች እና ምመናን ብቻ መኖር ምን ያህል ከቤ/ክ  እግዚአብሐየርም ከሆነ ከቃሉ ሚዛን እየራቀች  እንደሆነና ከተሰጣት ዋናው ተግባር እና ተልዕኮ ቀስ በቀስ   እየወረደች እና እያፈነገጠች  አሁን ባለችበት መንፈሳዊ  ለብታ  ላይ ደርሳለች፡፡

በሁላችንም እንደሚታወቀው የመጨረሻ ሰአት አልፈን የመጨረሻ መጨረሻ አላቂ ሰዓት ላይ እንዳለን የጌታ መምጣት በደጅ ከመሆን አልፎ በበር በሆነበት ዘመን ላይ መሆኑን እያወቅን ቤ/ክ ለሙሽራዋ በቃሉ በመንፈሱ በትክክል ራሷን ማዘጋጀት እና መዘጋጀት ሲገባት አሁን ግን በየመድረኩ ሙሽራይቱን የማያዘጋጁ ተግባራት እና ስብከት  ትምህርት መጠመዳችን በሁሉም የጌታን መምጣት በረሳ ህይወት በተዘረከረከ ማንነት እየተመላለስን የወደፊቱን የምድር የኑሮ ጥበቃ እውን ለማድረግ በራሳችን ነገር  ተይዘን እና ተጠምደን መታየትን እንደ መንፈሳዊ ስኬት እየቆጠርን  ባለንበት ዘመን ላይ ደረስን ኃጢያተኛን ኃጢያት ነው ብሎ መገሰፅ ባልተቻለበት ነገር ግን ህዝብ በብዙ ነገር  ተጠላልፎ ኃጢትን ማድረግ በለመደ በቆሻሻ ባደፈ ምንነት በተቀጣጠሉ ዝማሪዎች እና ዘመናዊ መሳሪያዎች በመታገዝ አምልኮን እንደ መዝናኛ ፔንክለር እየወሰደ እግዚአብሔርን እያመለከ እየመሰለው በዛው ማንነት የትንቢት ናዳ ሲዥጎደጎድለት ኃጢያትን ለምዶ ከአለም ጋር ወዳጅ ሆኖ እየተመላለሰ  ማንም ማንንም ተመለስ በማይልበት ሁኔታ  መድረኮቻችን በዘመናዊው እና ሰው ሰራሽ መንፈሳዊ በሚመስሉ   ትምህርቶች እና  አገልጋዮች ተውጠው  እውነት በውሸት ተተክቶ መድረክ አግኝቶ  ባልተለወጠ ሕይወት  የሚያሳፍረውን ነገር ባልጣለ ማንነት  አገልጋዮች ሎሎችን ለማገልገል  ለራስ ጥቅም ሲሯሯጡ  ህዝቡ የአጓጉል  ልማዶች  ሰለባ ሆኖ በየፕሮግራሙ ያዙኝ ልቀቁኝ ማለት  የተለመደ እንደሆነ ራሳችንን እና ሌሎችን እያሳትን በከንቱ ዘመናችንን እያባከንን  ወይ አልገባን ወይ አላስገባን ከልካይ ሆንን ለሎሌች መጥፋት እና ወደ ወንጌል እውነት ያለመምጣት ምክኒያት ሆነናል  የጌታን ስም አሰድበናል ፡፡

የመጨረሻ ሰዓት  የክርስቶስ መልዕክተኞች  አለማቀፍ አገልግሎት ከእግዚአብሔር በተሰጠው በተቀበለው ተልዕኮ ድርሻ ቤ/ክን  በዚህ መጨረሻ ሰዓት  እግዚአብሔር እንድትሆንለት   ወደ ሚፈልገው ወደ ታየላት መንፈሳዊ  መታደስ እና ከፍታ  እንደትደርስ የጊዜውን የእግዚአብሔርን የልብ ሀሳብ  በሁሉ አቅጣጫ በመግለጥ የጠፉትን ደህንነትን በሚሰጠው ወንጌል በመድረስ  ሁለንተናዊ አገልግሎት በመስጠት በቤቱ ያሉትን ለመንግስቱ እና ለምፃቱ የተዘጋጁ እንዲሆኑ በማስጠንቀቅ  በማሳሰብ በንቃት በትጋት የዝግጅት  መንፈስ ተላብሰው እንዲመላለሱ  መልክተኞች ሆነን የተላክንበትን የመልክተኛነት ተግባር በሁሉ አቅጣጫ በአገሪቱ ካሉ አብያተክርስቲያናት አጋር  በመሆን  በሁሉም ቦታ ከእውነተኛ የክርስቶስ ቤተክርስቲያን ጋር ተባብሮ በፍቅር መስራት ነው፡፡

አሁን  ቤተክርስቲያን ውስጥ ከሚታዩ ዘርፈ ብዙ  ክፍተቶች   አንፃር አገልግሎቱ አስፈላጊ ነው ብለን እናምናለን የጌታ መምጣት በደጅ መሆኑን ቀርቶ በበር በሆነበት ጊዜ ላይ እያለን ትንቢቶች ተፈፅመው የመምጣቱን  ዜና እያበሰሩ እየነገሩን ባሉበት ሰዓት ከእንቅልፍ የምትነሱበት ሰዓት አሁን እንደ ደረሰ ዘመኑን እወቁ ካመንበት ጊዜ ልቅ መዳናችን ዛሬ ወደ እኛ ቀርቧልና (ሮሜ 13፡11)

ንቁ ተዘጋጁ በመስጠት ጌታን አገልግሉት ተቀደሱ በፅድቅ  እየኖራችሁ  ሙሽራውንም ለመቀበል  ተነሱ ለምግስቱ ተዘጋጁ የሚሉን  ከመለኮት የተላኩ መልዕክተኞች ያስፈልጉናል ይብዙልን   ስለዚህ ምክኒያት እኛን ጌታ የመጨረሻ ሰዓት ምልዕክት ሰትቶን  ህዝቤን ለመንግስቴ እና ለምፃቴ አዘጋጁ ብሎ  መልክተኛ አድርጎን  ለትውልድ  ሁሉ ለቤተክርስቲያን የመምጣቱን አዋጅ ነጋሪ አድርጎን ይህንን አገልግሎት ሰቶናል እናተም ወንዶች እና  እህቶች ስለዚህ ራዕይ  ተፈፃሚነት በሁሉ አቅጣጫ ከጎናችን  በመሆን  ለእግዚአብሔር መንግስት ስራ አጋር ሆናችሁ እንድትተባበሩን በጌታ ፍቅር እንጠይቃለን፡፡

የመጨረሻ ሰዓት የክርስቶስ መልዕለኞች አለማቀፍ አገልግሎት