ከማይክል ሳምቦ መፅሐፍ ውስጥ በከፊል የተወሰደ

END time messangers ministry

የመጨረሻ ሰዓት መልዕክተኞች አገልግሎት

ተተርጉሞ ተዘጋጅቶ የቀረበ

 

“መንፈስ ለአብያተክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ “ ራዕይ 3፡22

 

ከማይክል ሳምቦ መፅሐፍ ውስጥ በከፊል የተወሰደ

 

 

 

 

 

 

 

 

 

ተርጓሚ- ወንድም ወ/አለማየሁ ጋሻው

2007

ጭሮ (አሰበ ተፈሪ)

 

ልጄ ሆይ የእኔ ቤተክርስቲያን አሁን ያለችበትን ሁኔታ ታውቃለህ; የእኔ ሙሽራ;እኔም ጌታ ሆይ አላውቅም ብዬ መለስኩ ጌታም ቤተክርስቲያኔ አሁን ያለችበት ሁኔታ አሳይሃለሁ አለኝ  እጁንም በምድር ወደ አንድ ወደ ተወሰነ ስፍራ ላይ  ሲያመለክት ነገሮች ሁሉ ከአይኔ ፊት ተነሱ እኔም ወደ ታች ሳይ ብዙ ህዝብ ተሰብስቦ ወደ አለበት ትልቅ መሰብሰቢያ አየሁ አዳራሹ ትልቅ ነው ህዝቡ  ተሞልቷል ምስጋና እና አምልኮ እየተካሄደ ነው  እኔም በአየሁት ነገር   ተገርሜ  ጌታ ሆይ በዚህ ቤተክርስቲያን ያሉ በእሳት በመንፈስ እና በእውነት እያመለኩ የአንተን መምጣት እየጠበቁ ነው ብዬ አልኩ

ወዲያው ይህን ስናገር የጌታ አይኖች በእንባ ተሞሉ አይደለም ልጄ ሆይ ተመልከት  ሲለኝ 1ሳሙ 10፡6,7 እኔም አተኩሬ ሳይ የሚያመሰግነው ያሚያመልከው ህዝብ በእስራት እንደሆነ አየሁ እጆቻቸው እግዞቻቸው ታስሯል በአንድነት በሰንሰለት ተያይዞ በአንገታቸው ላይ ባለ ብረት ጋር ታስሯል በአንገታቸው  ላይ ብረት አለ እያንዳንዱ በጭንቅላታቸው ላይ የሚከብድ  የኃጢያት ሸክም በላያቸው ላይ አለ ከዚህ የተነሳ አንገታቸው በአንድ ጎን ያዘመመ ነው

ሲታዩ  የደከሙ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ይመስላ አንዳዶች ፊታቸው በጭለማ በጥቁር የተወረሰ ነው በአንዳንዱ ፊት  ግንባር ላይ ትዕቢት፣ ክፋት፣ ዝሙት አለመታዘዝ ተለያዩ የኃጢአት አይነቶች ተጽፈውባቸዋል ማቴ 15፡7-9, ሕዝ 14፡2-3, ሕዝ 33፡30

እንደገና በጉባኤ መካከል አንድ ጥቁር የሆነ አካል ያለው የሚመስል ማንነት ወደ ላይ  ወደ ታች  እየተቀሳቀሰ በጉባኤው ውስጥ በእጁ ደረቱን እየመታ እየተኩራራ ይህ ህዝቤ ነው  እዚህ በእስራት ይዤ ጠብቄያቸዋለሁ አነርሱ እግዚአብሔርን እያገለገሉ እያመለኩ እየመሰላቸው ራሳቸውን ቤዛ አድርገዋል ግን አይደለም ይህን ስፍራ በፍጹም አይተውም  እያለ በትዕቢት በኩራ ይህን ይናገራል እኔ በሰማይ በዙፋኑ ፊት እየተከናወነ ካለው  አምልኮ ጋር አምልኮአቸው ምስጋናቸው  ብፍጹም አይገናኝም የተለያዩ  እና እጅግ በጣም መጥፎ እና የሚያስጠላ ነው  ለምን በንጹህ ልብ በእውነት በመንፈስ በቅድስና ከልብ የሚወጣ  ስላልሆነ በኋጢአት በእስራት ውስጥ ካሉ በሴይጣን ተፅእኖ ስር ከወደቀ ማንነት የሚወጣ አምልኮ እና ምስጋና ስለሆነ

ኢየሱስም አለኝ አሁን እንዳየኽው በቤተክርስቲያኔ ያለ ሁኔታ ነው እኔ ለአባቴ ለማቀርባት ያልኳት የፈለኳት  ቤተክርስቲያን ክበርት ንጽህት ያለነውር ያለለፊት መጨማደድ መሆን ሲገባት በተቃራኒው የባርነት የእስራት ብዙ ክፋቶች የሚሰሩባ ቦታ ሆነች ልጄ ቁጥር ስፍር የሌለው ክፋቶች አጸያፊ ነገሮች ሃጢያቶች ዛሬ በቤተክርስቲያኔ ውስት በህዝቤ በአገልጋዮቼ እየተሰሩ ነው የወንጌል አገልጋዮቼ   የተገለጠ ኃጢአት እየሰሩ እየተለማመዱ ለእኔ መስዋትን በተቀደሰ ስፍራ ላይ ይሰዋሉ እሳት ያነዳሉ

እንደ አሮን ልጆች እንግዳ እሳት ያልተፈቀ እሳት የእኔ ያልሆነ በፊቴ እያነደዱ ነው እንግዲህ  ከቤቴ ፍረድ የምጀምርበት ጊዜ ነው

የአይን ልጆች በፊቴ እንግዳ እሳት ሲያነዱ ካጠፋኋቸው እንዲሁ እነዚህንም አጠፋቸዋለሁ ነገር ግን እኔ የምህረት እምላክ ነን ሂድ አስጠንቅቃቸው ንገራቸው እምነታቸው እንዲጠብቁ በጽድቅ እና በቅድስና ደህንታቸው እንዲፈፅሙ ሂድና ስባኪዎችን አስጠንቅቃቸው በክፋታችሁ የምትመለሱበት ጊዜው አሁን እንደሆነ  ንገራቸው ንሰሃ ግቡ ብዙዎች ሃይሌን ክደዋል እኔን መምሰል ትተዋል በሰማይ ሁሉም ተዘጋጅቷል ተጠናቋል የቅዱሳኔን መነጠቅ ብቻ ነው የሚጠበቀው የእኔ ህዝብ ግን ዝግጁ አይደለም ቤተክርስቲያን ለሰማይ ነገር ዝግጁ አይደለችም እኔ የአባቴን ትእዛዝ ብቻ  እየጠበቅሁ ነው ቅዱሳኔን ለማምጣት የአባቴ ትዕዛዝ በምንም ጊዜ ይሁን በዚያ ጊዜ ጥቂት  ቅዱሳን ለንጥቀቴ የተዘጋጁ ቢሆኑ እንኳን እመጣለሁ ወደ ቤታቸው እወስዳቸዋለሁ

 

 

ጌታ ይባርካችሁ፡፡ ETM  አገልግሎት

ጌታ ኢየሱስ ይመጣል ሁል ጊዜ ተዘጋጅተህ ጠብቅ

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *