በተለያዩ እግዚአብሔር ሰዎች ስለ ንጥቀት  ያዩት ራዕይ በአንድነት የቀረበ

የመጨረሻ ሰዓት መልዕክተኞች አገልግሎት

ተተርጉሞ የተዘጋጅቶ የቀረበ

 

“መንፈስ ለአብያተክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ “ራዕይ 3፡22

 

በተለያዩ እግዚአብሔር ሰዎች ስለ ንጥቀት  ያዩት ራዕይ በአንድነት የቀረበ

 

 

 

ትርጉም- ወንድም ወ/አለማየሁ ጋሻው

 

የመነጠቅ ራእይ ከኤንጄሊካ ዘመባርኖ

ጌታችን ኢየሱስ ስለመንግስተ  ሰማይ እና ስለ ሲኦል  ብዙ ነገር ካሳያት ባሻገር ስለ ንጥቀት ክንውን አሳይቷታል እንዲህ አለኝ ጌታ ሲናገር “ ልጄ ወደ ምድር መመለስ አለበሽ አንድ ነገር አሳይሻለሁ፡፡

——-

ወደ ታልቅ እስክሪን እና በእስክሪኑ ላይ ህዝብን አየሁ አለምን ሁሉ ተመለከትኩ በድንገት በሺዎች የሚቆጠሩ ሲሰወሩ አየሁ እርጉዝ ሴት ከእነ እርግዝናዋ ስትሰወር ልጆች ህጻናት ከሁሉ ቦታ ሲሰወሩ ብዙ ሰዎች በሲቃ ወደዚያ ወደዚህ ይሄዳሉ  ይህ አይሁን! ይህ አይሁን! ምን እየሆነ ነው; ብለው ይናገራሉ

ጌታን ያውቁ የነበሩ ግን የቀሩትን አየሁ  ማቴ 24፡40-41 ክርስቶስ መጣ ንጥቀት ሆነ ብለው ይናገራሉ ራሳቸውን ለመግደል ይፈልጋሉ ግን አይችሉም በነዚያ  ጊዜያት ቀኖች ሞት ይሸሻል አለኝ  ጌታ በነዚያ ቀናት  መንፈስ ቅዱስ በምድር አይሆንም  በነዚያ ቀናት አደጋዎች ይሆናሉ ግን ሰዎች አይሞቱም

ሰዎች ከአንድ ቦታ ወደ አንዱ እየሮጡ እየጮኹ  ክርስቶስ መጣ ክርስቶስ መጣ ጌታ ሆይ ይቅር በለኝ ይቅር በለኝ ውሰደኝ ብለው ይለምና  ልመና ያቀርባሉ ግን በሃዘን ጌታ እንዲህ አለ  “ ጊዜው አልፏል”

ልጄ አሁን የንሰሃ ጊዜ ነው  ለሰዎች ሁሉ ሄደሽ እኔን እንዲፈልጉ ንገሪያቸው በዚያ ጊዜ የንሰሃ እድል የለም ኢሳ 55፡6 ልጄ  ለቀሩት ጊዜው ያለፈ  የመሸ ይሆንባቸዋል በንጥቀት ጊዜ  የሚቀሩትን ህዝብ ተመልክቶ ጌታ አለቀሰ እንዲህ አለ ልጄ ወደ ምድር ሄደሽ ንገሪያቸው  1ተሰሎ 4፡16-17 እንደተፃፈው

ግን ሁሉም ከጌታ  ጋር አይሄዱ ፍቃድ የሚያደርጉ ማቴ 7፡21 እና በቅድስና ሕይወት የሚኖሩ ጌታም  ተናገረኝ “ ቅዱስ የሆኑ ብቻ ናቸው ወደ መንግስቴ የሚገቡት ዕብ 12፡14 ጌታ ኢየሱስ  ይህን ብሎ ንግግሩን ፈፀመ “ የምመጣው ለቅዱስ ህዝብ ነው”

“ ሕዝቤ  የአለም ነገር ከእኔ አስበልጦ ተወኝ ህዝቤ ወደ መንገዴ ይመለስ እኔ የምመጣው ለቅዱስ ህዝብ ነው  ቅዱስ ህዝብ ብቻ እኔን ያያል የተዘጋጀ ያለነቀፋ ያለ እድፍ ያለ ነውር የሆነ ህዝብ ብቻ

 

 

ሊንዳ ኑወጃ ስለ ንጥቀት ያየችው ራዕይ

በየካቲት 15/2013 ዓ.ም ሞታ ዳግም በእግዚአብሔር ምህረት ሁለተኛ በምድር የመኖር እድል ያገኘችው ሊንዳ የሴራሊዮን ዜጋ ስትሆን ስለመንግስተ ሰማይ  ስለ  ሲኦል ካየችው ራዕይ ባሻገር ስለ ንጥቀት ያየችውን ጌታ የተናገራት እንዲህ ስትል  ትናገራለች ጌታ ኢየሱስ እንዲህ አለኝ “ እናተ ከጠበቃችሁት ከገመታችሁት  ጊዜ በፊት እመጣለሁ ቤተክርስትያኔን ግን ቆሽሻለች ለምን ቤተክርስትያኔ ቆሸሸች ዲያብሎስ ቤተክርስትያኔን  እንዲያቆሽሽ የረዱ ፓስተሮች አገልጋዮች ናቸው  ብዙዎች በቤተክርስትያን ከቃሌ ውጪ እና ማድረግ የማይገባቸውን  ነገሮች እያደረጉ ነው  በቤተክርስትያን የሚጠቀሙት ነገር ቤተክርስትያኔን አቆሸሹ

ተመልሳችሁ ለመምጣቴ የምትዘጋጁበት ጊዜ አሁን ነው

ዮዲላ ሳአወይር ስለ ንጥቀት ያየችው ራእይ

ጌታ እንዲህ አላት ጊዜው አብቅቷል  ጊዜው አብቅቷል የቀረ ሰአት የለም በቅርቡ በቅርቡ  ንጥቀት ይሆናል ፡፡

ሳሙኤል  አርቴጋ

በአስራዎች እድሜ  ውስጥ ያለ የናይጀሪያ ተወላጅ የሆነ ብላቴና አባቱ አገልጋይ የሆነ  በሰኔ መጨረሻ በሃምሌ መጀመሪያ 2013 ጌታ ብዙ ነገር ካሳየው በኋላ ካየው ራዕይ ውስጥ ስለንጥቀት ጌታ ያሳየውን  የነገረውን እንዲህ አቅርበናል

ሕዝቤን አስጠንቅቅ መምጣቴ ምፅአቴ ቀርቧል በአጠገብ ነው ንጥቀት እንደ ህልም ይሆናል  ለምጻቴ ተዘጋጁ

ጌታ ማቴ 24፡29-31 ሰጠኝ ሰዎች ሲነጠቁ ጌታን በአየር ሲገናኙ አየሁ ከመምጣቴ በፊት ጦርነት እና የመሬት መንቀጥቀጥ ይሆናል ፡፡

ሳሙኤል ጌታ እንደተናገረው በነዚህ ጊዜያት  ብዙ ጦርነቶች መሬት መንቀጥቀጦች ሆነዋል በአለም ላይ

የንሰሃ እድል አላችሁ ሰርጌ በአጠገባችሁ ቀርቧል ንሰሀ ግቡ ከመምጣቴ በፊት

በነብይ or ዴቪድ (David owour) ግንቦት 4/2014 ጌታ ስለምጸአት የነገረው

ጌታ በቤተክርስቲያን ባለመዘጋጀት ደረጃ በመሆኗ አዝኗል ፍጹም በእርሱ ራሷን ባለማሳደፍ ያለ እድፍ አይደለችም ያለ ነውር አይደለችም

ብዙዎች ከምፅአቴ ጋር ይተላለፋሉ ይቀራሉ ጌታ በሁሉ አቅጣጫ ባለመዘጋጀት ንጥቀት ስለሚያልፋቸው ስለሚቀሩ ቤተክርስቲያ አለቀሰ

ከዛንቢያ የሆነች እህት  ሪቸል ሙሸላ ስለ ንጥቀት ያየችው ራዕይ

Nov 5/ 2013

ጌታ እንዲህ አላት እኔ ቶሎ እመጣለሁ የእኔ መምጣት ሌባ በሌሊት እንደሚመጣ ነው በእውነት ለራሴ የሆኑትን አውቃቸዋለሁ ስለመምጣቴ ሰዎች ሲናገራቸው  ትኩረት አይሰጡም  የእኔ መምጣት  አይዘገይም  ከምታስቡት ጊዜ በፊት በቶሎ እመጣለሁ  ጥያቄው ተዘጋጅታችሃል እኔ የምመጣው ለቅዱስ ህዝብ ነው ቅዱስ ኑሮ የሚኖሩ ልጆቼ ብቻ ይነጠቃሉ ብዙ ክርስቲያኖች እኔ ስመጣ የተዘጋጁ አይደሉም ስለዚህ ቀሪዎች ናቸው አሁን በሩ ክፍት ነው  በቀርቡ ግን  ይዘጋል ከመዘጋቱ በፊት የሰው ልጆች ሁሉ የፍቅር እጆቼን ከፍቼ እየጠበቅሁ ነኝ

ዚፓራ ሙሽላ

ንጥቀት በአጠገባችሁ ነው ደረሰ ስለዚህ ራሳችሁን አዘጋጁ በአሁን ደቂቃ ብዙዎች እኔ እንዲህ በቶሎ ይመጣል ብዬ አላሰብኩም ይላሉ ብዙ ህዝቦች ንጥቀት የሚሆነው ከአመታት በኋላ ብለው  ያስባሉ ግን ንጥቀት ሲሆን ሁሉ ነገር ኖርማል ሆኖ ነው አንዳዶች በትምህርት ቤት ሳሉ በአንዳዶች  ቲቪ ሲያዩ ሲሸጡ ሲተኙ ምግብ ሲያዙ ሲበሉ  ወዘተ  ንጥቀት ይሆናል

በጣም ቅዱስ የሆኑ አገልጋዮች እንኳን ይቀራሉ ትንሽ ኃጢያት ነው  ብለው አስበው በኋላ አስተካክለዋለሁ ብለው ሳያስቡት በድንገት ንጥቀት ይሆናል ብዙዎች በቅድስናዬ መለኪያ  በሆነው ቃሌ ሲያመቻምቹ እና አለማዊ ሆነው ንጥቀት ይሆንባቸዋል

በፀሎት ፅኑ ቃሌን ስሙ አድርጉት ቃሉን  ለማጥናት ለፀሎት ራሳችሁን ስጡ አገልጋዮቼ በንቃት ፀልዩ የምመጣበትን ጊዜ አታውቁም  ፍሩኝ  ቀድማችሁ ራሳችሁን አዘጋጅታችሁ  ጠብቁኝ

 

ጌታ ይባርካችሁ፡፡ ETM  አገልግሎት

ጌታ ኢየሱስ ይመጣል ሁል ጊዜ ተዘጋጅተህ ጠብቅ

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *