“መንፈስ ለአብያተክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ “ ራዕይ 3፡22

END time massagers ministry

 

የመጨረሻ ሰዓት መልዕክተኞች አገልግሎት

ተተርጉሞ ተዘጋጅቶ የቀረበ

“መንፈስ ለአብያተክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ “ ራዕይ 3፡22

በውስጡ

የከርሜሎ በርኔስ የሲኦል ራዕይ

የእህት በርናርዳአ ፈራንዴዝ

በፓስተር ባራኒ ዲዮን

 

 

 

 

 

 

ተርጓሚ- ወንድም መ/አለማየሁ ጋሻው

2007

ጭሮ (አሰበ ተፈሪ)

 

ካርሜሎ በርኔስ በ1982 በመኪና አደጋ ምክንያት ሞቶ በጌታ ኢየሱስ ምህረት ሁለተኛእድል ተሰቶት ስለ ሲኦል ካየው  ራዕይ በከፊል የተወሰደ

በሲኦል ጌታ ያሳየውን ካርሜሎ በርኔስ ሲናገር እንዲህ ይላል

በሲኦል ፓስተሮችን ወንጌላውያንን  አማኞችን ሚሽነሪዎችን አየሁ እነዚህ በሲኦል ያሉት በተለያየ ኃጢያቶች ምክኒያት ነበር ከአየሁት ፓስተሮች ውስጥ አንዲ በመንፈስ ቅዱስ ሃይል  በልሳን መናገር በመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ፈፅሞ አያምንም በምድር አገልግሎቱ ወቅት አሁን ግን በሲኦል አጥብቆ ምህረትን ይለምና ጌታ አንድ እድል ይሰጠኝ ለአለም ሁሉ በልሳን መናገር  እውነትነት እና በመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት እውነት  መሆኑን ልናገር ግን ለእርሱ ይህ የዘገየ ልመና ነበር ከዚህ ስፍራ በምንም መውጣ አይቻልም ምክም ፓስተር ቢሆን ምክንያቱም ንሰሃ ማድረግ የሚቻለው በምድር በአካል ሲሆን ብቻ ነው ዕብ 9፡27

ሌላ ያየሁት ሚሽነሪ  በሲኦል የተገኘበት ምክንያ በአፍሪካ ለወንጌል ተልዕኮ  ለማድረግ ገንዘብ ሰብስቦ የገንዘቡን ግማሽ ለራሱ ያስቀረ ነበር በሲኦል የምህት እድል እንዲሰጠው ለምና ወደ ምድር  ሄዶ  ገንዘብን ለመመለስ  ነገር ግን ጌታ ኢየሱስ ሊረዳው አልቻለም ይህን ባየ ጊዜ ጌታን ኢየሱስን ረገመ

ሌላም ፓስተር አየሁ ከቤተክርስቲያን መባ እና አስራት እየሰረቀ ለራሱ ጥቅም  የሚያውል ለሰራው መጥፎ ስራ ምህረት ቢለምንም ሌላ እድል የለውም አገልጋዮች ምዕመናን ሁሉ ቆም ብላችሁ በጥንቃቄ እንድታስቡ የት ነው ፍጻሜዬን  የማሳልፈው ብላችሁ እንድታስቡ

ይህ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ሃልዎት መገኘት የምንሮጥበት ደህንነትን አጥብቀን የምንፈልግበት እምነታችን የምንጠብቅበት ጊዜ መሆን አለበት ስለ ራሳችን ጥሩ ስሜት እንዲሰማን የሚያደርጉን ደግደጉን እየመረጡ የሚነግሩንን በኃጢአታችን ምቾት እየተሰማን እንድንመላለስ የሚያደርጉንን ቤተክርስትያን  አትፈልጉ ነገር ግን የጌታ  መገኘት የሚንቀሳቀስበት እና በአጠቃላይ ሙሉ በሆነ የእግዚአብሔር ቃል ምክር የሚሰበክበት  ኃጢአትን በግልጥ አሳይተው እንድንናዘዝ ንሰሃ  እንድንገባ የሚያደርጉን ቤተክርስቲያን ፈልጉ ፍለጎታችን እየነገሩ ከነስተታችሁ  የሚተነብዩላችሁን  ለሲኦል ከሚያዘጋጁዋችሁ ራሳችሁን ጠብቁ

ወንድሞቼ በኃጢያት ውስጥ የምትመላላሱ ከሆናችሁ ነፍሳችሁ በአደጋ ውስጥ እንዳለች ልነግራችሁ እፈልጋለሁ

ብዙዎች ሰዎች ወዴት እንደሚሄዱ ግድ የላቸውም እንግዳ በሆኑበት በዚህ ምድር ራሳቸውን በኃጢያት በሚገኝ ጊዜያዊ  ደስታ ራሳቸውን ያታልላሉ በጣት ለሚቆጠሩ ዘመናት ብለው ዘላለማዊውን ይጥላሉ ይተዋሉ ይንቃሉ

በሲኦል ደግሞ አንዲት ሴት አየሁ ይህች ሴት ዩሐ 3፡16 የምታነብ ትመስላለች ኢየሱስ እሷ እዚህ የሆነችበት ምክኒያ ባለቤቷን ይቅር ማለት አቅቷት ነው አለኝ ማቴ 6፡14-15 ይህች ሴት ለሰላሳ አምስት አመት በቤተክርስቲያን ውስጥ በእረኝነት አገልግላለች አሁን ግን በሲኦል አንድ እድል እንዲሰጣት ባለቤቷን ይቅር ለማለት እንደተዘጋጀች ትናገራለች  ማቴ 5፡25 ማቴ 5፡7 ወገኖቼ ይቅርታ ማድረግ አስፈላጊ ነገር ነው ይህች ሴት ከ35 አመታት የእግዚአብሔር ቤት ስራ በኋላ  ፍጻሜዋን ለጥፋ አደረገች ወገኖቼ እርግጠኛ ሁኑ ሁሉንም የበደላችሁን ፈጥናችሁ ይቅር በሉ ይቅርታ በመስጠት ተመላለሱ በአገልግሎታችሁ የተነሳ ፈጽሞ ከመዘናጋት መንፈሳዊ ህይወታችሁን ቸል ከማለት  ስተታችሁን በምታገለግሉት አገልግሎት ከማካካስ  ተጠበቁ ካላችሁ የተከማቸ እውቀት ሳይሆን ከሕወታችሁ  አገልግሉ አገልግሎትን እንቅስቃሴ ሳይሆን  ህይወታዊ አድረውጋችሁ ይዛችሁት የእግዚአብሔር ፈቃድ ፈጽሞ የእግዚአብሄር ጸጋ የጌታ ኢየሱስ ጸጋ የመንፈስ ቅዱስ ህብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን አሜን

እህት በርናርዳአ ፍራንዴዝ ሁለት ጊዜ ወደ መንግስተ ሰማይ እና ወደ ሲኦል የሄደች ጌታ ኢየሱስ በራእይ ብዙ ነገር ያሳያት

ከምስክርነቷ በከፊል ተወስዶ የተተረጎመ

ጌታም ልጄ ሆይ በመጨረሻ ቀን ያለውን የህዝቤን መንፈሳዊ ሁኔታ  ላሳይሽ ነውና አሁን ለማሳይሽ ነገር ተጠንቀቂ

እኔም ክርስቲያኖች ደካማ ሆነው እና ድካማቸው አየሁ ጌታም እንዲህ ብሎ ጠየቀኝ  ቤተክርስቲያኔ አሁን ባለችበት በዚህ ሁኔታ በእኔ ልትወሰድ ትችላለችን አለኝ;

እንዲህ ብሎ ነገረኝ ከእኔ ጋር የሚሄዱ ክርስቲያቾች በክብሬ የተሞሉ ባለድሎች ያለነቀፋ የሆኑ  የተዘጋጁ ብቻ ናቸው አሁን በህዝቤ መካከል ውሸት ተለምዷል ፍቅር የለም ህዝቤ ተከፋፍሏል የልብ አንድነት የለውም ባለፉት ዘመናት ያለችዋን የእኔ ቤተክርስቲያን እንዴት ትኖር እንደነበር አሳይሻለሁ አለም  እነዚህ ልጆቼ በመንፈሴ ክብር የተሞሉ ነበሩ በቋሚነት ይጾሙ ይጸልዩ ነበር ቃሌን ተሞልተው በድፍረት ያለፍርሃት በሁሉ ቦታ ይሰብኩ ነበር

በአሁን ዘመን ያሉ ክርስቲያኖች እኔም መንፈሴም የተለወጥን መስሏቸው ያስባሉ እኔ መንፈስም አልተለወጥንም

ትልቁ በዚህ ቀን ያሉ ክርስቲያቾች ስህተት በሰባዊነት የታቀደ ድግግሞሽ አስልቺ የሆነ የተለመደ እንደ ቃሌ እንደ መንፈሴ ያልሆነ ሕይወት እየኖሩ ያገለግላሉ  ከላይ ያለውን የመንፈስ ቀዱስ መልዕክት ዘንግተውታል

ለፓስተሮች ለአገልጋዮች ንገሪያቸው ከተለመደ ከተደጋገመ አሰልቺ ከሆነ የራሳችሁ ፕሮግራሞቻችሁን ስርአቶቻችሁን የምትጥሉበት የምትተውበት በመንፈሴ ፕሮግራም ውስጥ የምትገቡበት ጊዜው አሁን ነው  ይህን ካደረጋችሁ የመንፈስ ቅዱስ ሃይል በመካከላችሁ ሲገለጥ ታያላችሁ  በዚህ መጨረሻ ሰአት እንዳለፈችው ቤተክርስቲያን ብዙ ድንቆችን ታአምራቶችን ሙታንን ማስነሳት በመካከላችሁ አደርጋለሁ መንፈሴ ዛሬም ያው ነው እናተ ተለውጣችሁ እንጂ ብዙዎች ቃሌን ይሰብካሉ እንደ ቃሌ ግን አይኖሩም ቃሌን እንደተጻፈው ስበኩ  ስበኩ አስተምሩ ለራሳችሁ ጥቅም ቃሌን አታጣሙ አትቀንሱ  ጠላት ጥቂት ጊዜ እንዳለው አውቆ  በህዝቤ ላይ ውጊያ ከፍቷል ህዝቤ ይህን እያስተዋለ አይደለም ተዘናግቷል ጠላት በዝሙት መንፈስ ብዙ ባሪያዎቼን አጥቅቷል ጥሏቸዋል ባርያዎቼ እንዲወድቁ ያደረገበት የሆነበት ምክኒያት ክብሬን ለእኔ አልሰጡም ክብሬን ሰረቁ 1 ጢሞ 2፡11-14

የጠላት ጥቃት ቢጨምርም ከእኔ ጋር የተጣበቁ የተስማሙ ምንም አይሆኑም የእኔ ጥበቃ በእነርሱ ዙርያ ስለሆነ

ህዝቤ ሆይ ነቅታችሁ ልብሳችሁ ጠብቁ ልብሳችሁን የረሳችሁ ያስቀመጣችሁ  ያለበሳችሁ ፈጥናችሁ ልበሱ ያቆሸሻችሁ ፈጥናችሁ በደሜ ታጠቡ

ወገኖቼ መንፈስ ቅዱስ ልብሳችሁን በንጽህና እንድትጠብቁ እንዲረዳችሁ አብዝታችሁ ጠይቁ ህብረታችሁን ከእርሱ ጋር አድርጉ

ከጌታ የተሰጡ ስድስት መልክቶች  ለቤተክርስቲያ በፓስተር በሪኒ ዱዮን

  1. ለሕዝቤ እንዲህ ብለህ ንገር በፍጹም ልባችሁ ሀሳባችሁ ሃይላችሁ በእኔ እመኑ እነዚህ የሚጨነቁ እና የሚጠራጠሩኝ እዚህ ወደ መንግስቴ አይገቡም
  2. ወደ ቤተክርስቲያን በታማኝነት በፕሮግራሞች በሰአቱ ተገኙ ለምን ይህ ጊዜ ፊቴን ብርሃን በህዝቤ ላይ የማበራበት እና ወገኖቼን የሚያበት ጊዜ ስለሆነ ህዝቤ ልጆቼ በቤተክርስቲያን በአንድነት በንጽህና በእውነት ሲያመልከኝ እደሰታለሁ
  3. በጸሎታችሁ ታማኞች ሁሉ በቃሌ ኑሩ ፍቃዴን አድርጉ
  4. ልጆቼ በአስራታቸው እና በመባቸው ታመኞች ታዛዦች እንዲሆኑ ንገራቸው  የሰማይ  ያለው  ቤታቸው የሚሰሩበት አንዱ ግባአታቸው ስለሆነ
  5.   ለሕዝቤ ንገራቸው የምድር ሃብታቸውን ያላቸውን ገር በጸሎት ሙሉ በሙሉ ለእኔ  እንዲያስረክቡ  ለጥበቃ እና ለበረከት ራሳቸውን በምድር ባለ ነገራቸው እንደይጠበቁ ይጠንቀቁ  ስመጣ እንደዚህ እንዳላገኛቸው የሎጥን ሚስት አስቧት
  6. ለልጆቼ ንገራቸው ሁል ጊዜ በንቃት ራሳቸውን አዘጋጅተው እንዲጠብቁኝ ምክንያቱም በቅርብ እመጣለሁ ሰዎች ከሚጠብቁት ጊዜ በፊት

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *